አማርኛ እርዳታ እና እገዛ : Trosolwg
የህዝብ ቆጠራው ምንድነው?
የህዝብ ቆጠራው በየ 10 ዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን፣ ኢንግላንድ እና ዌልስ ውስጥ ያለውን የህዝብና ቤተሰብ ስዕል በመረጃ ያሳያል። የሚቀጥለው የህዝብ ቆጠራ እሁድ ማርች 2021 ይካሄዳል።
ከህዝብ ቆጠራው የሚሰበሰበው መረጃ፣ የቋንቋ አገልግሎቶችን ጨምሮ በየአካባቢው የሚሰጡ የህዝብ አገልግሎቶችን ለማቀድ እና በጀት ለመመደብ ይረዳል። ለምሳሌ ብሄራዊ የጤና አገልግሎት (NHS) በተለዩ ክልሎች በጽሁና በንግግር የትርጉም አገልግሎቶች መስጠት ያስፈልገው ይሆናል።
The Office for National Statistics (የብሄራዊ ስታስቲክስ ቢሮ)(ONS) ኢንግላንድ እና ዌልስ ውስጥ የህዝብ ቆጠራውን ያቅዳል፣ ያካሂዳል።
ማን ነው የህዝብ ቆጠራውን መሙላት ያለበት
የህዝብ ቆጠራው ስለእርሰዎ እና ስለቤተሰበዎ ጥያቄዎችን ይጠይቃል፣ ኢንግላንድ እና ዌልስ ውስጥ የሚኖር እያንዳንዱ ሰው መሙላቱም በጣም አሰፈላጊ ነው።
በህጉ መሠረት የህዝብ ቆጠራዉን መሙላት አለበዎ
የተሳሳተ መረጃ መስጠት እና የህዝብ ቆጠራውን አለመሙላት ህግ መጣስ ሲሆን እስከ £ 1,000 ሊያስቀጣዎት ይችላል። አንዳንዶቹ ጥያቄዎች በፈቃደኛነት የሚመለሱ መሆናቸው በግልጽ ተቀምጧል። እነኝህን ጥያቄዎች ባይመልሱ ህግ መጣስ አይሆንም።
ከሶስት ወር ላነሰ ጊዜ በዩኬ ውስጥ ስለመቆየት
በዩኬ ውስጥ ከሶስት ወር ላነሰ ጊዜ የሚቆዩ ከሆነ የህዝብ ቆጠራውን የመሙላት ኃላፊነት የለበዎትም። ያሉበት ቤተሰብ ኃላፊ አንዳንድ ጥያቄዎችን ሊጠይቁዎት ይችላሉ፣ ይህንንም በማድረግ በቤተሰቡ ውስጥ ስለቆዩት (ስላረፉት)ሰዎች በህዝብ ቆጠራው ውስጥ ሊሞሉ ይችላሉ።
የህዝብ ቆጠራዎትን መቼ እንደሚሞሉ
ሁሉም ቤተሰብ የህዝብ ቆጥራውን እሁድ፣ ማርች 21 ቀን 2021 ወይም ከዚያ በኋላ በተቻለ ፍጥነት መሙላት አለበት።
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ሁኔታዎች ተቀይረው ይሆናል። አሁን ያሉበት ሁኔታ ላይ ተመስርተው ለጥያቄዎቹ መልስ ይስጡ።